Kebado Town, Dara Wereda, Sidama Region +251 466 600 516/431 info@ktvet.edu.et Mon-Fri: 8:30 AM - 5:30 PM
በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚከናወኑ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምርምር ሥራዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተገለጸ ቀባዶ፡ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም | Kebado TVET College

News Detail

Read full story from Kebado TVET College

Back to News
በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚከናወኑ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምርምር ሥራዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተገለጸ ቀባዶ፡ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚከናወኑ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የምርምር ሥራዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተገለጸ ቀባዶ፡ ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ቴክኖሎጂን የመቅዳትና ለኅብረተሰቡ የማሸጋገር፣ እንዲሁም በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ችግሮችን የመፍታት ተግባራት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጉልህ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ተጠቆመ።

ይህ የተገለጸው ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም በቀባዶ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ በተካሄደው የ2018 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር መድረክ ላይ ነው።
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ከፍያለው ከበደ እንደገለጹት፤ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጆች ውስጥ የሚመረቱና የኅብረተሰቡን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው።
አቶ ከፍያለው አክለውም፣ በኮሌጁ ውስጥ ተሠርተው ለውድድር የቀረቡት ቴክኖሎጂዎችና ተግባራዊ የጥናት ምርምር ሥራዎች የአካባቢውን ማኅበረሰብ ችግሮች ከመቅረፍ አኳያ ተስፋ ሰጪና አበረታች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
በመድረኩ ላይ የተገኙት የክብር እንግዶችና የዕለቱ ታዳሚዎች በበኩላቸው፣ በኮሌጁ ውስጥ በተለይም በግብርናው ዘርፍ የሚሰጡ የሙያ ሥልጠናዎች ተግባር ተኮር እንዲሆኑ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል። ከሥልጠናው ጎን ለጎን የኮሌጁን የውስጥ ገቢ ለማሳደግ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትም እጅግ አመርቂ መሆናቸውን በምልከታቸው አረጋግጠዋል።
ለውድድሩ የዳኝነት ሥራ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙት ምሁራን፣ የቀረቡትን የፈጠራና የጥናት ሥራዎች በአካል በመገምገም ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ ሲሆን፣ በደረጃቸው መሠረትም ለይተው አሳውቀዋል።