Kebado Town, Dara Wereda, Sidama Region +251 466 600 516/431 info@ktvet.edu.et Mon-Fri: 8:30 AM - 5:30 PM
የቀባዶ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የፈጠራ ስራዎችን ባበረከቱ አሰልጣኞች ላይ የዕውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም አካሄደ | Kebado TVET College

News Detail

Read full story from Kebado TVET College

Back to News
የቀባዶ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የፈጠራ ስራዎችን ባበረከቱ አሰልጣኞች ላይ የዕውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም አካሄደ

የቀባዶ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ የፈጠራ ስራዎችን ባበረከቱ አሰልጣኞች ላይ የዕውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም አካሄደ

ቀባዶ (ሰኔ 29/2018 ዓ.ም) — በቀባዶ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ማህበረሰባዊና ተቋማዊ ችግሮችን መፍታት የሚያስችሉ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለፈጠሩና በውድድሩ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ አሰልጣኝ መምህራን በዛሬው እለት (ሰኔ 29 ቀን 2018 ዓ.ም) የገንዘብ እና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበረከተ።

ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት በተለያዩ የፈጠራ ዘርፎች የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ያወዳደረ ሲሆን፥ ከደረጃ 1ኛ እስከ 3ኛ የወጡት የፈጠራ ስራዎች የሚከተሉት ናቸው፡

1ኛ ደረጃ፡ በአሰልጣኝ መምህር ዘነበ ተስፋዬ የተሰራው "የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን"፤

2ኛ ደረጃ፡ በአሰልጣኝ መምህር ይስሃቅ ይልማ የተዘጋጀውና ተቋማዊ አሰራርን የሚያቀላጥፈው "Web-based TVET Management Portal"፤

3ኛ ደረጃ፡ በአሰልጣኝ መምህር አብርሃም ሙቁራ የተሰራው "የአሸዋ ማጣሪያ ማሽን"።

እነዚህን ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁ የፈጠራ ባለቤቶች የተዘጋጀላቸውን የገንዘብና የሰርተፍኬት ሽልማት ከኮሌጁ የሥራ ኃላፊዎች እጅ ተረክበዋል። በተጨማሪም በውድድሩ ላይ ተሳትፈው የተለያዩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ያቀረቡ ሌሎች አሰልጣኝ መምህራንም ላበረከቱት አስተዋጽዖ የዕውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

ይህ የሽልማት ፕሮግራም መምህራን በተግባራዊ ምርምርና በፈጠራ ስራዎች ላይ ያላቸውን ተነሳሽነት ይበልጥ እንደሚያሳድገውና ለቀጣይ ስራዎች ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር በዕለቱ ተገልጿል።